መረጃ

Your internet is very weak.
የእርስዎ ኢንተርኔት በጣም ደካማ ነው።
ናትካ ኢንተርነት ብዙሕ ደካማ እዩ።
nternet kee baaxô daciifa.
በትዕግስት ይጠብቁ!

loading 05-04-2026 17:17pm

የግዳን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የጋራ ፎረም ዉይይት አካሄደ ቀን 15/7/2018 ዓ.ም(ግዳን ወረዳ ኮሙኒኬሽን)

የግዳን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የጋራ ፎረም ዉይይት አካሄደ ቀን 15/7/2018 ዓ.ም(ግዳን ወረዳ ኮሙኒኬሽን) የጋራ ፎረም ዉይይቱ የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤትን ተጋባዥ በማድረግ የተካሄደ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት ከተከናወኑት ተግባራት መካከል 34 የይዞታ ማረጋገጫ መሰጠቱን፣112 የስመ ንብረት ዝዉዉር ስራ መሰራቱን ፣ተቋሙ ገቢ በመሰብሰብ ለልማትና ለተቋሙ ሰራተኞች ደመወዝ የሚከፍል እንደመሆኑ መጠን ከልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 29ሚሊዮን 734ሽ ብር ለመሰብሰብ አቅዶ በ8 ወራት ዉስጥ 1ሚሊዮን 969 ሽ 850 ብር መሰብሰቡን የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመድ ቢረዳ አሳዉቀዋል፡፡ በዉይይቱ የተሳተፉት የጋራ ፎረም አባላት በበኩላቸዉ መዘጋጃ ቤቱ ፅዳትና ዉበት ላይ በትኩረት መስራት አለበት፣ለህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ መስጥት ያስፈልጋል፣በዚህ ዓመት የጎርፍ ማስወገጃን ጨምሮ ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ለማከናወን ምን ታስቧል፣የመሰረተ ልማት ፍትሃዊነት ችግር አለ፣አረንጓዴ ልማት ላይ በትኩረት መሰራት አለበት እንዲሁም ገቢ ከተሰበሰበ በኋላ ተጨባጭ የሆነ ስራ ሰርቶ ለህብረተሰቡ ማሳየት ያስፈልጋል የሚሉ ሃሳብና ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመድ ቢረዳ ከፎረም አባላቱ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት ገቢ በሚፈለገዉ ልክ መሰብሰብ ካልተቻለ ሁሉም የልማት ጥያቄዎች ሊመለሱ እንደማይችሉ አሰገንዝበዉ ሙጃ ከተማን ለማዘመንና የፀዳች ለማድረግ ለተቋሙ ወይም ለመዘጋጃ ቤቱ ብቻ ሳይሆን የሚመለከታቸዉ ተቋማትና የከተማዉ ነዋሪዎች ትብብርናኃለፊነት የላቀ መሆን ስላለበት ሁሉም የሚጠበቅበትን ግዴታ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ይህ ዘገባ የተነበበው 8ጊዜ ነው

Comment Form