መረጃ

Your internet is very weak.
የእርስዎ ኢንተርኔት በጣም ደካማ ነው።
ናትካ ኢንተርነት ብዙሕ ደካማ እዩ።
nternet kee baaxô daciifa.
በትዕግስት ይጠብቁ!

loading 05-04-2026 17:40pm

የግዳን ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የ2014 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም እና የ2015 እቅድ ትውውቅ ፕሮግራም አካሄደ

በፕሮግራሙ ላይ የወረዳው አስተዳዳሪ ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ፣ ባለሙያዎች ፣ የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ፣ የወንዳች እና የደንሳ ታዳጊ ከተሞች ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ተሳታፊ ሁነዋል ፡፡ በዚህም በ2014 በጀት ዓመት በጥንካሬ የታዩ የሥራ አፈጻጸም በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሻለ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ፣ የአገልግሎት ችግሮችን በአፋጣኝ ሁኔታ መፍትሄ እንዳገኙ መደረጉ ፣ ከአጋር አካላት ጋር ያለው ትስስር ጠንካራ መሆኑ በጥንካሬ የሚታዩ ሲሆን በድክመት ደግሞ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ አለመዘጋጀቱ ፣ የፅዳት ቀን ቢወሰንም በተከታታ አለመተግበሩ ፣ በሁሉም ከተሞች ሞዴል መንደር አለመፈጠሩ እና የሙጃ ከተማ እድገት በአንድ አቅጣጫ መሆኑ እንዲሁም ቤት ለመገንባት የተደራጁ ማህበራትን በሰዓቱ ምሪት መስጠት አለመቻሉ ዋናዋናዎቹ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በቀጣይ በጀት ዓመት ለመስራት ከታቀዱት መካከል 500 ሜትር የኮብልስቶን ንጣፍ ስራ፣1ከ.ሜትር የመንገድ መብራት ግንባታ ፣ሶስቱን ከተሞች የአስተዳደር ወሰን እንዲኖራቸው ማድረግ ፣ደረጃውን የጠበቀ የደረቅ ቆሻሻ ቦታ ማዘጋጀት ፣ የህዝብ ተሳትፎን በተሻለ መልኩ ማሳደግ ፣ ያለአግባብ የተያዙ መሬቶችን ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ ማድረግ ዋናዋናዎቹ ሲሆኑ መሰረተ ልማትን በሚፈለገው ልክ ለመገንባት 9ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ እንዳለበት የወረዳው ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቡድን መሪ አቶ ተመስገን ብርሃን ተናግረዋል፡፡

ይህ ዘገባ የተነበበው 2ጊዜ ነው

Comment Form