05-04-2026 17:46pm
የግዳን ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት የሙጃ ወንዝ ድልድይ ተገንብቶ መጠናቀቁን ገለጸ
ቀን23/7/2013ዓ.ም የግዳን ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት የሙጃ ወንዝ ድልድይ ተገንብቶ መጠናቀቁን ገለጸ ለበርካታ ዘመናት የወረዳዉ ህዝብ ጥያቄ ሆኖ የነበረዉ የሙጃ ወንዝ ድልድይ ግንባታ የካቲት 6/2012ዓ.ም ተጀምሮ በአንድ አመት ከሁለት ወር ጊዜ ዉስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ግንባታዉም የተከናወነዉ በአማራ ክልል መንገድ ትራንስፖር ቢሮ በጄት እንደሆነ በመግለጽ ለግንባታዉ የወጣ ወጭም ቫትን ሳይጨምር 18 824 529.49(አስራ ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃያ አራትሺ አምስት መቶ ሃያ ዘጠኝ ብር ከአርባ ዘጠኝ ሳንቲም)ሲሆን ከቫት ጋር ለግንባታ የዋለ ጠቅላላ ወጭ 21 648 208.91(ሃያ አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ስምንትሺ ሁለት መቶ ስምንት ብር)ከዘጠና ሳንቲም እንደሆነ የግዳን ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት የፕሮጄክት ኮንትራት አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ደመወዝ ሃብቱ ተናግረዋል፡፡ ድልድዩም 42 ሜትር ስፓን ስፋት ያለዉ እንደሆነ እና በዩራፕ ከተገነቡት ድልድዮች በጣም የተሻለ በመሆኑ ያለምንም ስጋት 50 አመት እንደሚያገለግል በመግለጽ የድልድዩ መገንባትም 04፣06፣07እና08 ቀበሌዎችን ከማገናኘትም በተጨማሪ ከላስታ ወረዳ ሁለት ቀበሌዎችን ከሙጃ ከተማጋር በማስተሳሰር ከፍተኛ ጥቅም ያለዉ ቢሆንም አሁን ላይ አገልግሎት መስጠት እንደማይችል የተናገሩት ቡድን መሪዉ ለዚህም ዋናዉ ምክኒያት ወደ ድልድዩ የሚወስደዉ 320 ሜትር የመንገድ ቆረጣ ስራ ባለመስራቱ እንደሆነገልጸዋል፡፡
