መረጃ

Your internet is very weak.
የእርስዎ ኢንተርኔት በጣም ደካማ ነው።
ናትካ ኢንተርነት ብዙሕ ደካማ እዩ።
nternet kee baaxô daciifa.
በትዕግስት ይጠብቁ!

loading 05-04-2026 17:47pm

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሃሳብ በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ የአቅመ ደካሞች ቤትን የመጠገን ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሃሳብ በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ የአቅመ ደካሞች ቤትን የመጠገን ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ሙጃ : ሃምሌ 17/2017 ዓ,ም ( ግዳን ወረዳ ኮሙኒኬሽን) በሙጃ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች አቅመ ደካሞችን የማገዝ እና ከችግር የማውጣት ስራ ተጠናክሮ እየተሠራ ይገኛል ፤ በዚህም የቤት ጥገና አገልግሎት በተጠናከረ መንገድ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው እለት አንድ የአቅመ ደካማ ቤት የማደስናየመጠገን ተግባር ተፈፅሟል። የግዳን ወረዳ ወጣትናስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ እና የክረምት በጎ ፈቃድ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ፈንታ በየነ እደተናገሩት በተግባሩ የተሳተፉትን የ01 ቀበሌ አመራሮችን እና የሙጃ ከተማ ኗሪዎችን እድሁም በገንዘብናበጉልበት አስተዋጽኦ ለአበረከቱ በሙሉ ምስጋና አቅርበው ከዛሬው ስራ በተጨማሪም ሌሎች ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ኮሚቴው አሁንም ሀብት የማፈላለግ ስራ እየሰራ ስለሚገኝ ሁሉም ህብረተሰብ በቅን ልቦና አጋዥ እንዲሆን በማለት አቶ ፈንታ በየነ ጥሪ አስተላልፈዋል። "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"!!

ይህ ዘገባ የተነበበው 4ጊዜ ነው

Comment Form