05-04-2026 17:50pm
በመትከል ማንሰራራት"! በሚል መሪ ሃሳብ በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ሀገር አቀፍ የአንድ ቀን ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተጀመረ
ሙጃ፡ ሃምሌ 24/2017ዓ,ም (ግዳን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን) በመርሐ_ግብሩ የግዳን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል አያሌው ፣ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ባዩህ፣ የወረዳ ስራ አስፈፃሚዎች ፣ የወረዳ አመራሮች ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ የሙጃ ከተማ ኗሪዎች እንድሁም በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል። በተከላው 300 ሄ|ር መሬት በአንድ ጀንበር ይሸፈናል ፣ 3.1 ሚ/ቁ ችግኝ በአንድ ጀንበር ለመትከል መታቀዱን ፣ ለዚህም ችግኞች ተዘጋጅተው መቅረባቸውን እና በዛሬው እለት ተተክለው የሚጠናቀቁ መሆኑን የወረዳው ግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን ሞላ አስታውቀዋል። "በመትከል ማንሰራራት"!!
