"Please wait"
እባክዎ በትዕግስት ይጠብቁ የኢንተርኔትዎ ዳካማ መሆን ነው!

✕ Home About Us Main point Service Job Vacancy Comment

በግዳን ወረዳ የሙጃ ከተማ የመነሃሪያ ግንባታ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለ

05-04-2026 17:53pm

ቀን8/8/2013ዓ.ም
በግዳን ወረዳ የሙጃ ከተማ የመነሃሪያ ግንባታ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
የሙጃ ከተማ መነሃሪያ ግንባታ የወረዳዉ መንግድ ትናስፖርት ጽ/ቤትና ሙጃ መሪ ማዘጋጃ ቤት ክትትል እና ቁጥጥር እየተገነባ ሲሆን ለግንባታዉም 400000(አራት መቶ ሽ)ብር ወጭ እንደተደረገ በመጠቆም አሁን ላይ መነሃሪዉ በመጠናቀቅ ላይ እንዳለ ተገልጿል፡፡
ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ለመጀመር ዉስጡን መደልደል፣የእንግዳ ማረፊያ መገንባት ፣የልስን እና የግርፍ ስራ እንደሁም የድምድማት ስራዎች እንደቀሩት በመግለጽ እነዚህን በአጭር ጊዜ በመጨረስ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ቀልጣፋና የተሸለ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸዉን የግዳን ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አረጋ በላይ ተናግረዋል፡፡
መነሃሪያዉ ሲጠናቀቅ የትራንስፖርት ህግን ለማስከበር እና ለማክበር ትልቅ አስተዋጽኦ ያለዉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ታሪፍ መነሃሪያ ዉስጥ እንዲከፈል ይደረጋል ተሽከርካሪዎች በስምሪታቸዉ መሰረት እንዲወጡ ይሆናል፣ሁሉም ተሽከርካሪዎች መነሃሪያ ዉስጥ ያድራሉ፣ ያለ ስዓት የሚወጣ ተሽከርካሪን ለመቆጣጠር ምቹ ሁኔታዎች ይፈጠራሉ በጫኝ እና አዉራጅ እንዲሁም በድለላ ስራ ለሚሰማሩ ወጣቶች የስራ ዕድል እንደሚፈጠር በመግለጽ መነሃሪያዉ የወረዳዉ ህዝብ ንብረት ስለለሆነ ህብረተሰቡ በባለቤትነት ሊጠብቀዉና ሊንከባከበዉ እንደሚገባ አክለዉ አሳስበዋል፡

loading

ይህ መረጃ 32 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇    ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form