"Please wait"
እባክዎ በትዕግስት ይጠብቁ የኢንተርኔትዎ ዳካማ መሆን ነው!

✕ Home About Us Main point Service Job Vacancy Comment

የግዳን ወረዳ ርዕሰ መዲና ሙጃ ከተማ ታሪክ

02-05-2026 17:31pm

የሙጃ ከተማ ታሪክ በአጭሩ ሲታይ
የግዳን ወረዳ ርዕሰ መዲና ሙጃ ከተማ የተመሰረተችው በ1902 ዓ.ም ሲሆን ሙጃ የሚለው ስም የመጣው ሙጃ የሚባል ሳር በብዛት የሚበቅልባት አካባቢ በመሆኗ ሲሆን ከጎንደር ወረታ ጋይንት የሚመጡ የጨው ነጋዴዎች ቆቦ ጨው ለመነገድ ሙጃን አቋርጠው ይሄዳሉ በዚህ ጊዜ ነጋዴዎቹ ማደሪያችን ያች ሙጃ ሳር የሚበቅልባት ቦታ ነች ብለው ከሁለቱም ቦታ ሲመላለሱ ማደሪያቸው አድርገዋት ስለነበር በዚህ ምክንያት ሙጃ ብለው አወጡላት፡፡
ሙጃን ለመጀመሪያ ጊዜ የቆረቆሯት ሰው ደጃች ሀይሉ ወ/ኪሮስ ይባላሉ፡፡ ይህ ሰው በመጀመሪያ ቤት አድርገው የቆረቆሩበትም በአሁኑ ጊዜ የመድሃኒአለም ቤተክርስቲያን የተሰራበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ሰው በ1913 ከሞተ በኋላም ቤተሰቦቹ ቦታውን ይዘውት ይኖሩበት ነበር፡፡ ከዛም በመቀጠል ሙጃ ከመቆርቆር አልፋ ወደ ከተማነት ስትሻገር ይህ ቦታ የከተማዋ የቀበሌ ጽ/ቤት ሆኖ ያገለግል ነበር፡፡ ሙጃ ወደ ወረዳነት ስትለወጥ ቦታው የወረዳ ፍ/ቤት፣ ፖሊስ ጽ/ቤት የማ.ክ.ሰ.ማ የእጅ ስራ ማሰልጠኛ በመሆን አገልግሏል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታም ሙጃ መድሀኒአለም ቤተክርስትያን ተሰርቶበት እያገለገለ ይገኛል፡፡
በ1928 ዓ.ም ሙጃ ወደ ወልዲያ መውጫ ልዩ ቦታው ዙሮበር የሚባል ቦታ ላይም ጣልያን ካምፕ ሰርተው ይኖሩበት ነበር፡

ይህ መረጃ 11 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇    ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form