በሰሜን ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ ለወረዳዉ የፀጥታ ሃይል የከተማ ቦታ ርክክብ መደረጉ ተገለፀ
14-07-2026 07:20amቀን14/10/2018ዓ.ም
በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ ለወረዳዉ የፀጥታ ሃይል የከተማ ቦታ ርክክብ የተደረገ ሲሆን የዚህ ዕድል ተጠቃሚ የሆኑት የሚሊሻ፣የፖሊስ እና በሰላም ማስከበር ስራ ላይ የተሰማሩ አካላት መሆናቸዉን የግዳን ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ እንዳወቅ አለልኝ ተናግረዋል፡፡
ም/ኃላፊዉ አክለዉ አስተዳደር ምክር ቤቱ፣የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት እና የሚመለከታቸዉ አካላት በቅንጅት በመስራት ለፀጥታ ሃይሉ ይህንን በማድረጋቸዉ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል፡፡
የግዳን ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ በየነ እንደተናገሩት የወረዳውን የፀጥታሀይል የቦታ በለቤት ለማረግ 109 የፀጥታ ሀይሎችን በ5 ማህበር በማደራጀት የአለባቸውን የቤት ችግር ግምት ውሰጥ በማሰገባት መሰፈቱን እንዲያሟሉ አግዛ በማድረግ የቤት መስሪያ ቦታውን ማስረከብ ተችሏል ብለዋል።
የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመድ ቢረዳ እንደገለፁት የፀጥታ ሃይሉ የቤት መስሪያ ቦታ እንዲያገኝ ከክልል በተሰጠዉ አቅጣጫ መሰረት ከመሬት ፅ/ቤት፣ከህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት እንዲሁም ከወረዳዉ አስተዳደር ም/ቤት ጋር በመቀናጀት በ7 ሄክታር መሬት በ5 የቤት ማህበራት ለተደራጁ የወረዳዉ ፀጥታ አካላት ቦታ የማስተላፍ ስራ ተሰርቷል ያሉ ሲሆን በዚህ ሂደትም 128 አርሶ አደሮች እስከ ልጆቻቸዉ ቦታ እንደተጠበቀላቸዉ ገልፀዉ ይህን ዕድል የሚያገኙት ልጆች ከዚህ በፊት በስማቸዉ ቤት የሌላቸዉና እድሜያቸዉ ከ18ዓመት በላይ የሆኑት ብቻ መሆናቸዉን አስገንዝበዋል፡፡
ዋና ስራ አስኪያጁ አክለዉም የካሳ ስሌትን በተመለከተ ምንም አይነት ችግር የለም ያሉ ሲሆን ቅሬታ አለኝ የሚል አረሶ አደር ካለ ግን መብቱ ስለሆነ ለሚመለከተዉ አካል ጥያቄዉን ማቅረብ እንደሚችል ጠቁመዉ ወደ ካሳ ስሌት ከመገባቱ በፊት ለአርሶ አደሩ ሰፊ ግንዛቤ መፈጠሩንም አስታውሰዋል፡፡
የከተማ ቦታ ሲረከቡ ያገኘናቸዉ የወረዳዉ የፀጥታ አካላት በበኩላቸዉ የከተማ ቦታ በላቤት በመሆናችን በጣም ደስ ብሎናል ያሉ ሲሆን የረጅም ጊዜ ጥያቄያችን ተመልሶልናል በማለትም ገልጸዋል፡፡
ይህ መረጃ 53 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----
ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇 👇 👇 ሚዲያወች በመጫን Share..
