መረጃ

Your internet is very weak.
የእርስዎ ኢንተርኔት በጣም ደካማ ነው።
ናትካ ኢንተርነት ብዙሕ ደካማ እዩ።
nternet kee baaxô daciifa.
በትዕግስት ይጠብቁ!

loading 05-04-2026 17:42pm

በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ የአስተርዮ ማርያም አመታዊ ክብረ-በዓል በድምቀት ተከበረ

ቀን22/5/2015ዓ.ም በግዳን ወረዳ ሙጃ ከተማ የአስተርዮ ማርያም አመታዊ ክብረ-በዓል በድምቀት ተከበረ የአስተርዮ ማርያም ክብረ-በዓል በየአመቱ ጥር 21 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የእረፍት ቀን ምክኒያት በማድረግ በታላቅ ድምቀት የሚከበር ሲሆን የዘንድሮዉ ክብረ-በዓል እንደ ስከዛሬዉ ሁሉ ሌላ ቦታ የሚኖሩ የአካባቢዉ ተወላጆች ፣ከተለያየ ቦታ የመጡ ካህናት አባቶች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት በሊቃዉንት ወረብ ፣በሰንበት ተማሪዎች መዝሙር ፣በሆታና ጭፈራ ሃይማታዊ ትዉፊቱን ጠብቆ በድምቀት መከበሩን በቦታዉ ተገኝተን መመልከት ችለናል፡፡ የሙጃ ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክንፈ ገብርኢል ፀጋየ እንዳሉት ይህ በዓል በየአመቱ ከቅርብም ከሩቅም በሚመጡ ህዝበ ክርስቲያን የሚከበር መሆኑን አስታዉሰዉ የሙጃ ከተማ ወጣቶች አካባቢያቸዉን በማፅዳት፣የእንግዶችን ማረፊያ በማመቻቸት እንዲሁም ከተማዋ ያማረ ድባብ እንዲኖራት ላደረጉት ርብርብ ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ በዓሉን ከዚህ በተሻለ ለማክበርና ለማስተዋወቅ እንግዶችን በተለመደዉ ሁኔታ በፍቅር መቀበል፣አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች ማለትም አልጋ ቤቶች፣ሆቴልና ምግብ ቤቶች ፣የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች የሚጠበቅባቸዉን ኃላፊነት እንዲወጡ በመጠቆም በዋናነት የህዝብ ግንኙነት ስራዉ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡ ይህ ሃይማኖታዊ በዓል ሙጃ ላይ በተለየ መልኩ የሚከበርበት ምክኒያት ሙጃ ማሪያም ጥንታዊትና ታሪካዊ ቦታ በመሆኗ፣ብዙ ቅዱሳን የፀለዩባት እና ያረፉባት እንዲሁም በተሰጣት ቃል ኪዳን የለመኗትን ሁሉ ስለት የምታደርስ ስለሆነች እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ቦታዉ ትልቅ ክብር ተሰጥቶት መስቀል በጉራጌ፣ገና በላሊበላ ፣ጥምቀጥ በጎንደር በልዩ ሁኔታ እንደሚከበረዉ አስተርዮ በሙጃ በሀገር ደረጃ እዉቅና አገኝቶ ሃይማኖታዊ ትዉፊቱን እንደጠበቀ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆን ጉዳዩ ለሚመለከታቸዉ አባቶች ማሳወቅ፣የወረዳዉ መንግስትና ህዝቡ በመቀናጀት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ቄ/ዮሓንስ እሸቴ ተናግረዋል፡፡

ይህ ዘገባ የተነበበው 8ጊዜ ነው

Comment Form